አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2011 የኢፌድሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሀመትን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ እና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሀመት በነበራቸው ቆይታም በአፍሪካ ወቅታዊ ጉዳዮችና ምሰራቅ አፍሪካ ሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

ከዚህ ባለፈም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ መሀመት ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በፕሬዚዳንትነት  በመመረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ በመልካም መኞታቸው ገለጸውላቸዋል።

ሊቀመንበሩ ሙሳ ፋቂ መሀመት ከውይይቱ በኋላ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥  ፕሬዝዳንት ሳሀለወርቅ ዘውዴ በአፍሪካ እና በኢትዮጵያ ባለቸው ዲፕሎማሲያዊ ስኬት በአህጉሪቱ ስኬታማ ለውጥን እንደሚያመጡ እተማመናለሁ ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *