አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 28፣ 2011  የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ  ዘውዴ  በአፍሪካ የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ለመካፈል ወደ ደቡብ አፍሪካ አቀኑ ።

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ  በሚሳተፉበት ፎረም ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት፣ ኢንቨስተሮች እና ሌሎች ሌሎች ተቀማት ይገኛሉ ተብላል።

የኢንቨስትመንት ፎረሙ  በአህጉሪቱ  የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለማስፋት ይረዳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፥ ኢትዮጵያም ያላትን የኢንቨስትመንት ዕድል በ ፎረሙ ላይ ታስተዋውቃለች ተብሎ ይጠበቃል።

የአፍሪካ አንቨስትመንት ፎረም ከዛሬ ጀምሮ ለተካታታይ ሶስት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል።

ፕሬዘዳንት ሳህለወርቅ  ወደ ሀላፊነት ከመጡ  ለሁለተኛ ጊዜ የሚያደርጉት የውጭ ሀገር ጉዞ ነው።

Comments are closed.