አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 17 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ4 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የርብ ግድብ በነገው እለት በይፋ ይመረቃል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር በፋርጣና እብናት ወረዳዎች መካከል የተገነባው ርብ ግድብ 800 ሜትር ርዝመት እና 73 ነጥብ 5 ሜትር ከፍታ አለው።

234 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ የመያዝ አቅም ያለው ይህ ግድብ፥ 20 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ማልማት የሚያስችል ነው ተብሏል።

ፕሮጀክቱ በአካባቢው ያሉ አርሶ አደሮች የግድቡን ውሃ በመጠቀም በዓመት ሶስት ጊዜ የተለያዩ ሰብሎችን እንዲያለሙ ያስችላቸዋልም ነው የተባለው።

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የፕሮጀክቱ ተቋራጭ ሲሆን፥  የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ደግም የማማከር ስራውን አከናውኗል።

የግድቡ ግንባታ በ2000 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን በተለያዩ ምክንያቶች በእጅጉ በመዘግየቱ፥ የተያዘለት በጀት በሶስት እጥፍ አድጎ በነገው እለት በይፋ ይመረቃል።

1 ሺህ ሄክታር መሬት የሚሸፍነው ፕሮጀክት በ1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር እንዲገነባ ቢታቀድም የገንዘቡ መጠን በየጊዜው እየተሻሻለ አጠቃላይ 4 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጎበታል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *