ሰኔ 5/10/10 ዓ. ም ( ዓባይ ኤፍ ኤም )

ጅቡቲ የነበሩ 361 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ መደረጉ ተገለፀ።

ኢትዮጵያዊያኑ ስደተኞች በህገ ወጥ ደላሎች አማካኝነት በጅቡቲ አድርገው ወደ አረብ ሀገራት ለመሄድ ወደ ጅቡቲ የገቡ መሆናቸው ተገልጿል።

ከተጨማሪም የመን ውስጥ ባለው ጦርነት ምክንያት ከየመን ወደ ጅቡቲ የመጡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መሆናቸውን ተነግሯል።

ስደተኞቹ በጅቡቲ የሚገኘው የኢፌዲሪ ኤምባሲ እና በዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት የጋራ ጥረት ወደ አገራቸው ገብተዋል።

ቀሪዎቹ 24 ስደተኞች ደግሞ ነገ እንደሚገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ከዚህ በፊት የመንን አቋርጠው ወደ ተለያዩ የአረብ አገራት ለመሄድ ፈልገው የነበሩ እና የየመንን ጦርነት ሸሽተው ወደ ጅቡቲ የተመለሱ ከ1 ሺህ 700 በላይ ኢትዮጵያዊያንን ባለፉት ዘጠኝ ወራት ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ይታወሳል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *