ሰኔ 01/10/10 ( ዓባይ ኤፍ ኤም )
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በኡጋንዳ ለሚያደርጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ካምፓላ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ኢንቴቤ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኦሪዬም ኦኬሎ እና የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ግብዛ ወደ ኡጋንዳ ያቀኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት እና ባለስልጣናት ጋር በሁለትዮኝ እና አህጉራዊ ጉዳዮች ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የኡጋንዳ ጉብኝታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ግብፅ እንደሚያመሩ ይጠበቃል።
በኡጋንዳ በሚያደርጉት ይፋዊ የስራ ጉብኝት በሀገሪቱ 29ኛው ብሄራዊ የጀግኖች በዓል እንደሚታደሙ ታውቋል።
በዚህ ብሄራዊ በዓል ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ለአፍሪካ እና ለኡጋንዳ መልካም ስራ ለሰሩ ሰዎች ሀገሪቱ የምታበረክተውን ሜዳሊያ በፕሬዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ ይበረከትላቸዋል ተብሏል።
ይህ ሽልማት በተለያዩ ጉዳዮች አስተዋፅኦ አበርክተዋል ተብለው ለተመረጡ አፍሪካዊ መሪዎች የኡጋንዳ መንግስት የሚበያበረክተው ሽልማት እንደሆነም ተገልጿል።
የሀገሪቱ ፕሬዚዳነት ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው በዚህ ብሄራዊ በዓል ኡጋንዳ ለሀገራቸው በጀግንነት በጎ አስተዋፅኦ ላበረከቱ 250 የሚጠጉ ሰዎች ሜዳልያ ይሰጣል።
ኡጋንድ ይህን የብሄራዊ የጀግኖች በዓል ከፈረንጆቹ 1989 ጀምሮ ለሀገራቸው ነፃነት፣ ሰላም እና ዴሞክራሲ ራሳቸውን አሳልፈው ለሰጡ ዜጎች እውቅና ለመስጠት በየአመቱ የምታከብረው ብሄራዊ በዓል ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *