ግንቦት 30/09/10 ( ዓባይ ኤፍ ኤም )
የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጅን ይቭስ ለድርየን አገራችንን ይጎበኛሉ፡፡
በነገው እለት አዲስ አበባ የሚገቡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በቆይታቸው ከኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽዮ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ፡፡
የፈረንሳይ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡
5ኛው የኢትዮ ፈረንሳይ የቢዝነስ ፎረም በዚህ ዓመት መጋቢት ወር ላይ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወሳል፡፡
121 የፈረንሳይ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶች በአገራችን የተመዘገቡ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 65ቱ በስራ ላይ ይገኛሉ፡፡
ፈረንሳይ የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ አጋር ስትሆን በሁለቱ አገሮች መካከል የተጀመረው ግንኙነት አንድ ምዕተ ዓመትን ሲያስቆጥር ግንኙነቱ የተጀመረው በ1890 ዓ.ም በአፄ ምንሊክ ዘመን ነው፡፡
ምንጭ፡- የውጪ ሚ/ር የቃል አቀባይ ፅ/ቤት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *