ግንቦት 30/09/10 ( ዓባይ ኤፍ ኤም )
የተጀመረዉን ልማትና ሰላም ለማስቀጠል ከመቼዉም ጊዜ በላይ ጠንክሮ እንደሚሰራ የአዲስ አበባ ከተማ ኦህዴድ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
ጽ/ቤቱ ከአዲስ አበባ የኦህዴድ አባላት ጋር የልማትና የሰላም ኮንፈረንስ አካሂዷል፡፡ ኮንፈረንሱ በአባ ገዳዎች ምርቃት የተጀመረ ሲሆን ለትግሉ ለተሰዉ ሰማዕታትም የህሊና ፀሎት ተደርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ኦህዴድ ጽ/ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ፈይሳ አሰፋ ኮንፈረንሱ ከወረዳ ጀምሮ ሲካሄድ የነበረ መሆኑን ገልፀዉ እስካሁን ሲሰሩ የነበሩ ተግባራት ጥንካሬ እና ክፍተቶችን ከአባላቱ ጋር መገምገሙ ለቀጣይ ዉጤታማ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡
በዉይይቱ የተከናወኑ ተግባራት ጠንካራ እና የነበሩ ክፍተቶች የሚል ፅሁፍ ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል፡፡
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ፣ የኦሮሚያ ክልል እና የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ አመራሮችና የድርጅቱ አባላት ተሳትፈዋል፡፡
ምንጭ፡- አዲስ አበባ ኮምንኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *