ግንቦት 30/09/10 ( ዓባይ ኤፍ ኤም )
ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል 20 ቴሌቪዥኖችን ለመሰጠትና ማዕከሉን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ ቃል ተገባ ፡፡
የኢፌዴሪ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚንስትር አመራሮችና ሰራተኞች የመቄዶኒያ የአረጋውያንና አዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከልን ግንቦት 29/2010 ዓ.ም ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ በማዕከሉ ከፍተኛ ፍቅርን እንዳዩ ገልጸዉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በአንድ ወር ውስጥ 20 ቴሌቪዥኖችን በስጦታ እንደሚያበረክቱ እና የማዕከሉን እንቅስቃሴ በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የሚያስችሉ ስራዎችን ለመስራት ቃል የገቡ ሲሆን ከመስሪያ ቤቱ ማህበረሰብ በተውጣጣ ገንዘብ የተገዙ የጽዳት መገልገያዎች በጉብኝቱ ወቅት ለማዕከሉ አበርክተዋል ፡፡
በጉብኝቱ ወቅት የኢፌዴሪ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር አመራሮችና ሰራተኞች ማዕከሉን በሚችሉት መንገድ እንዲደግፉ የኢፌዴሪ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ሚንስትር ዴኤታው ዶ/ር ሽመቴ ግዛዉ ጥሪ አቅርበዋል ፡፡
ምንጭ፡- የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚ/ር

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *