ግንቦት 8/09/10 ዓ.ም ( ዓባይ ኤፍ ኤም )
የኢትዮጵያ የሱዳን እና የግብፅ የውጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ፣ የውሀ ሀብት ሚንስትሮች እንዲሁም ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሀላፊዎች በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከአንድ አመት በላይ ያደረጉት እልህ አስጨራሽ ውይይት ትላንት ምሽት በስኬት መጠናቀቁን የውጪ ጉዳይ ሚ/ር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
በመዲናችን አዲስ አበባ በተካሄደው ስብሰባ ላይ ሶስቱ አገሮች የሶስትዮሽ መሠረተ ልማት ፈንድ ለማቋቋም፣ የታላቁ የህዳሴ ግድብን የውሃ አሞላል የሚያጠና ብሔራዊ ገለልተኛ የአጥኝዎች ቡድን ለማቋቋም ፤ ለአማካሪ ድርጅቱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶችን ለማቅረብ ተስማምተዋል።
በስብሰባው መክፈቻ ላይ የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ የሶስትዮሽ ውይይቱ ውጤታማ እንዲሆን በሙሉ ልብ ትሰራለች ማለታቸው ይታወሳል።
ምንጭ፡- የውጪ ጉዳይ ሚ/ር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *