ግንቦት 8/09/10 ዓ.ም ( ዓባይ ኤፍ ኤም )
የስድስት ቀናት ጉብኝት የሚያደርጉት ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፥ በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ኪሪል ግብዣ ነው ወደ ሩሲያ ያቀኑት።
ጉብኝታቸውን ትናንት ግንቦት 7/ 2010 ዓ.ም.በሩሲያ በይፋ የጀመሩት ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ከሩሲያ ተጠባበቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።
በውይይታቸውም የሩሲያው ተጠባበቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ፥ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያናት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነትን ሞስኮ በበጎ መልኩ እንደምትመለከተው አብራርተዋል።
ሁለቱ ቤተክርስቲያናት በዓለም ዙሪያ መቻቻል እና ሰላም እንዲሰፍን በማድረግ ላይ የበኩላቸውን ሚና መጫወት እንደሚችሉም ላቭሮቭ ተናግረዋል።
ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ እና ሰርጌ ላቭሮቭ ባደረጉት ቆይታም በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለው የጠበቀ ታሪካዊ ግንኙነት የበለጠ ማሳገድ በሚቻልበት መንገድ ላይ ከመምከራቸውም በተጨማሪ በዓለም ላይ ስጋት የሆነውን ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ዓለም አቀፍ ማህበረሰብን ባሳተፈ መልኩ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል።
ምንጭ ፡- በሞስኮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *