ግንቦት 8/09/10 ዓ.ም ( ዓባይ ኤፍ ኤም )

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ እንደሻው ጣሰው ለጋዜጠኞች ትላንት በሰጡት መረጃ እንደገለፁት በከተማዋ ከዘጠኝ መቶ ሺ በላይ ተማሪዎች የሚገኙ መሆናቸውን ገልጸው ተማሪዎቹ ተገቢውን የትምህርት አገልግሎት እንዲያገኙ ቢሮው በተማሪዎች ውጤት ፣ ስነ ምግባር ፣ የመምህራን ሙያ ማሻሻያና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የመምህራን ሙያ ፍቃድ ፤ የፅሁፍ ምዘና አሰጣጥ ፣ የግል ትምህርት ተቋማት ኢንስፔክሽን ስርዓት ፣ የፈተና ኩረጃ በትምህርት ጥራት ላይ ያለው ተጽዕኖ ፤ የተማሪዎች የጎዳና ላይ ሩጫ ቅድመ ዝግጅትና ሌሎች በትምህርቱ ዘርፍ ትኩረት የተሰጣቸውን ጉዳዮች ትምህርት ቢሮው ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረጉን ነው አቶ እንዳሻው የገለጹት፡፡
ህብረተሰቡ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ከመላክ ባሻገር በመማር ማስተማሩ ሂደት ላይ ጠንካራ ተሳትፎና ድጋፍ ሊያደረግ ይገባል ያሉት የትምህርት ቢሮው ሃላፊ በተለይ በትምህርት ልማት ስራ ላይ መገኛኛ ብዙሃን የሚጫወቱት ሚና የጎላ በመሆኑ በጋራ ተናበን መስራት አለብን ሲሉም አሳስበዋል፡፡
ምንጭ፡-የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ኮሚዩኒኬሽ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *