ግንቦት 8/09/10 ዓ.ም ( ዓባይ ኤፍ ኤም )

በብሩንዲ ህገ መንግስታዊ ማሻሻያ የሚጠይቀውን ህዝበ ውሳኔ ለማካሄድ ቀጠሮ ተይዟል፡፡
በዚህም መሰረት ህዝበ ውሳኔው በአሁኑ ወቅት ያለው የሀገሪቱ ህገ መንግስት ፕሬዝዳንት ፒየሪ ንኩሩንዚዛ በፈረንጆቹ 2020 በሚደረገው ምርጫ ለመወዳደር የማያስችላቸው መሆኑን ተከትሎ የስልጣን ጊዜያቸውን ለማራዘም ያለመ ነው በሚል እየተተቸ ይገኛል፡፡
እ.ኤ.አ በ2005 ከ5 አመት ወደ 7 አመት የተራዘመው የፕሬዝዳንቱ የስልጣን ዘመን የመጨረሻውን እና በውዝግብ የተሞላውን ምርጫ በ2015 እንዲያካሂዱ አስችሏቸው እንደነበረ የሲጂቲኤን ዘገባ ያስታውሰናል፡፡
በመሆኑም ፕሬዝዳንት ንኩሩንዚዛ ሀገሪቱ በ2020 ለምታካሂደው የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዲሳተፉ ለማመቻቸት የተዘጋጀው ህዝበ ውሳኔ በመስማማት ከተጠናቀቀ፣ፕሬዝዳንቱ እ.ኤ.አ እስከ 2034 ድረስ ብሩንዲን ለመምራት የሚያስችላቸውን በር ይከፍትላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ለዚህ ህዝበ ውሳኔም 5ሚሊየን ብሩንዲያውያን በሀገሪቱ የምርጫ ኮምሽን በኩል ተመዝግበዋል ሲል ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

( ምንታምር ፀጋው )

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *