ግንቦት 8/09/10 ዓ.ም ( ዓባይ ኤፍ ኤም )

የአልጣያር የውጭ ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ በህገወጥ መንገድ ፈቃድ ወስዶ ዜጎችን ወደ የውጭ አገር ስራ ላይ ከማሰማራቱም በተጨማሪ ፈርስት ቱር ኤንድ ትራቭል ከተባለ የጉዞ ወኪል ጋር ግንኙነት እንዳለው ከቀናት በፊት ኢቲቪ ባስተላለፈው ዘገባ መገለፁ ይታወሳል፡፡
ይህ ተግባር የውጭ ስራ ስምሪት አዋጅ ላይ የተቀመጠውን ክልከላን የሚተላለፍ በመሆኑ የመናዊ ዜግነት ያላቸዉ የፈርስት ቱር ኤንድ ትራቭል የጉዞ ወኪል የስራ ሀላፊዎችን ጨምሮ ሁለት ተጠርጣሪዎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቱሪስት ቪዛ አማካኝነት ወደ አረብ ሀገራት በተለይም ወደ ሳዉድ አረቢያ የሚደረገዉን ህገወጥ ጉዞ በማቀነባበር ወንጀል ተጠርጥረዉ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ አስታውቋል፡፡
ፖሊስ በተጠርጣረዎቹ መኖሪያ ቤትና ቢሮ ባደረገው ፍተሻ የተለያዩ ፓስፖርቶችንና የጉዞ ሰነዶችን መያዙንም ገልጿል፡፡
ከፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ኮማንደር ከተማ ደባልቄ በሰጡት መረጃ ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ በመተላለፍ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ውስጥ ተሳታፊ ከሆኑ አካላት መካከል የህክምና ተቋማት እንዳሉበት ጠቁመዋል፡፡
ምንጭ፡- ኢቢሲ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *