(የካቲት 5 – 2010)

የሃገር መከላከያ ሰራዊት አባላትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ውይይት በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ቦታዎች እየተካሄደ ነው።

ለ6ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሃገር መከላከያ ሰራዊት ቀን ምክንያት በማድረግ “ሰላማችን የህዳሴ ጉዟችን አጠናክሮ ያስቀጠለ የህዝብ ፍቅርና አመኔታ ያተረፈ የድል ሰራዊት” በሚል መሪ ቃል በመዲናዋ አምስት ቦታዎች ውይይት እየተደረገ ነው።

በመዲናዋ ጃን ሜዳና አካባቢው የሚገኙ የሰራዊት አባላት፥ “ህዝባዊ ባህሪያችን እያጎለበትን ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በመጠበቅ የሃገራችን ህዳሴ በመጠበቅ ዋስትና ሆነን እንቀጥላለን” በሚል መሪ ቃል ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ጋር እየተወያዩ ነው።

የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ዋና አዛዥ ሜጄር ጀኔራል ሃለፎም እጅጉ፥ የሃገር መከላከያ ሰራዊት ህዝብና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ የሰጠውን አደራ በብቃት ለመወጣት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

ለውይይቱ የመነሻ ፅሁፍ ቀርቦ የቀረበ ሲሆን፥ ጽሁፉ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ከተደራጀበት የአጼ ቴዎድሮስ ዘመነ መንግስት እስካሁን ያለውን ሂደት ለመቃኘት ሞክሯል።

ህዳር 29 ቀን 19 87 ዓ.ም ህብረ ብሄራዊ መከላከያ ሰራዊት ተቋቁሞ፥ የሃገሪቱ ብሄር ብሄረሰቦች ተዋጽኦ እንዲኖረው መደረጉም በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።

ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ግንባታው ሃገራዊ ቅርጽና ይዘት ኖሮት እንዲቋቋም መደረጉም በዚህ ወቅት ተጠቅሷል።

በውይይቱ ወቅት ሰራዊቱ የህዝብና የመንግስት የመሰረተ ልማት አውታሮችን በመጠበቅ ረገድ ያደረገው አስተዋጽኦ ተጠቅሷል።

ከዚህ ባለፈም ስርዓት አልበኝነትን በመጠበቅ፣ ፀረ ሰላም ሃይሎችን በመግታትና በመቆጣጠር፣ የሃገሪቱን ዳር ድንበር ከውጭ ወራሪ ሃይሎች በመካከልና በጎረቤት ሃገራት

ሰላም በማስከበር በአለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ሰራዊት ማፍራት መቻሉም ተገልጿል።

ሰራዊቱ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ከመጠበቅ ባለፈ በተለያዩ የልማት ስራዎች ተሳትፎ ማድረጉም ነው በውይይቱ ወቅት የተገለጸው።

በዚህም ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 1 ቢሊየን ብር የሚጠጋ ቦንድ ግዥ በመፈጸም፥ ለአቅመ ደካሞች ደግሞ 65 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ድጋፍ በተለያዩ ወቅቶች አድርጓል ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም 192 ሚሊየን ብር በሚጠጋ ወጭም ለወላጅ አልባ ህጻናት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፥ በአካባቢ ጥበቃ ስራና በሌሎች መስኮች ድጋፍ ማድረጉም ተነስቷል።

ውይይቱ ሰራዊቱ የተቋቋመው ለህዝቡ እንደመሆኑ መጠን ከህዝቡ ጋር ያለውን ቁርኝት ከፍ ለማድረግ ያለመ ሲሆን፥ ሰራዊቱም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት እያደረገ ነው።

ምንጭ

(ኤፍ.ቢ.ሲ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *