(ታህሳስ 21 – 2010)

ብሔራዊ የደረጃዎች ምክር ቤት 500 የኢትዮጵያ ደረጃዎችን አፅድቋል።

የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያዘጋጃቸውን 500 የኢትዮጵያ ደረጃዎችን ነው በብሄራዊ የደረጃዎች ምክር ቤቱ በ22ኛ መደበኛ ሰብሰባው ያፀደቀው።

በጠቅላላው በስድስት ዘርፎች 568 የኢትዮጵያ ደረጃዎች ለምክር ቤቱ የቀረቡ ሲሆን፥ ከነዚህ መካከል 500 ደረጃዎች ብሄራዊ ደረጃዎች እንዲሆኑ ፀድቀዋል።

ከነዚህ ውስጥ 241 አዲስ፣ 118 የተከለሱ፣ 141 በማስቀጠል፣ የፀደቁ ደረጃዎች ናቸው።

በዚህ መሠረት የፀደቁት የኢትዮጵያ ደረጃዎች የሚከተሉት ናቸው፦

• በግንባታና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ዘርፍ 51 አዲስ፣ 29 የተከለሱ፣ 20 በማስቀጠል በድምሩ 100 የኢትዮጵያ ደረጃዎች

• በአከባቢና ጤና ደህንነት ዘርፍ 6 አዲስ፣ 13 የተከለሱ፣ 1 በማስቀጠል በድምሩ 20 የኢትዮጵያ ደረጃዎች

• በኤሌክትሮ ሜካኒካል የደረጃ ዝግጅት ዘርፍ 116 አዲስ የኢትዮጵያ ደረጃዎች

• በመሠረታዊና አጠቃላይ የደረጃ ዝግጅት ዘርፍ 46 አዲስ ፣ 20 በክለሳ፣ 6 በማስቀጠል በጠቅላላው 72 የኢትዮጵያ ደረጃዎች

• በግብርና ምግብ የደረጃ ዝግጅት ዘርፍ 7 አዲስ፣ 12 የተከለሰ፣ 28 በማስቀጠል በድምሩ 47 የኢትዮጵያ ደረጃዎች

• በኬሚካልና ኬሚካል ውጤቶች 15 አዲስ፣ 44 የተከለሱ፣ 86 በማስቀጠል በድምሩ 145 የኢትዮጵያ ደረጃዎች

በአጠቃላይ የፀደቁት ደረጃዎች ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖራቸው የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ አስታውቋል።

ደረጃዎቹ የምርቶችንና የቁሳቁሶችን እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮችን ጥራት ከማሻሻልና ከማረጋገጥ አንፃር ለኢንዱስትሪው ክፍለ ኢኮኖሚ በተለይም ለማምረቻው ኢንዱስትሪና ለንግድ የተወዳዳሪነትን አቅምን ሊያጎለብቱ እንደሚችሉ ታምኖባቸዋል።

እንዲሁም ለቴክኖሎጂ ሽግግርና ለፈጠራ ስራ፣ ለህብረተሰቡ ጤናና ደህንነት፣ ለአካባቢ ጥበቃ እና የሸማቾች ጥቅምን ለማስጠበቅ እንደሚረዱ የኤጀንሲው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ምንጭ

(ኤፍ.ቢ.ሲ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *