(ታህሳስ 21፣ 2010)

በልማት ተቋማት ላይ የሽብር ድርጊት ለመፈጸም የጦር መሳሪያ ታጥቀው ከሶማሊያ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ የሽብር ቡድን የሆነው የኦጋዴን ብሄራዊ ነጻነት ግምባር /ኦብነግ/ 2 አባላት በፅኑ እስራት ተቀጡ።

ቅጣቱን ያስተላለፈው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሾቹ 1ኛ አህመድ አብዲ እና 2ኛ አህመድ መሃመድ አወል በሞቃድሾ ነዋሪ የነበሩ ሲሆን፥ ከሶማሊያ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት በፖሊስ ሃይል ላይ ተኩስ በከፈቱበት ወቅት ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

የፌዴራል የድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት አቃቤ ህግ ክስ እንደሚያመላክተው ተከሳሾቹ የሽብር ድርጊት ለመፈጸም ሃምሌ 8 ቀን 2008 ዓመተ ምህረት ከኦብነግ ስድስት የሽብር ቡድን አመራሮች ጋር በመሆን መሳሪያ በመታጠቅ ከሶማሊያ ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው በክሱ ተጠቅሷል።

በርሞ ጎግ በሚባል አካባቢ በሚገኙ የፖሊስ ሀይል አባላት ላይ ተኩስ ሲከፍቱ ከነመሳሪያቸው በቁጥጥር ስር ውለዋልም ይላል።

የግራ ቀኙን ክርክር የመረመረው ችሎቱ ተከሳሾቹ አቃቤ ህግ ያቀረበባቸውን የሰነድም ሆነ የሰው ምስክር ማስተባበል ባለመቻላቸው ጥፋተኛ በማለት 1ኛ ተከሳሽን በ13 አመት ፅኑ እስራት እና 2ኛ ተከሳሽን በ15 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።

ምንጭ

(ኤፍ.ቢ.ሲ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *