(ህዳር 16፣ 2010)

250 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት ኤንኤ ሜታል ኢንዱስትሪ እና ኢንጅነሪንግ ዘመናዊ የከባድ ጭነት ተሳቢ(የትሬይለር) ማምረቻ እና የሲኖትራክ መገጣጠሚያ ፋብሪካ ዛሬ ተመርቋል።

ፋብሪካው አዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ለቡ ኢንዱስትሪ ዞን ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፥ ግንባታው ለመጨረስም 3 ዓመት መውሰዱን የድርጅቱ ባለቤት እና ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ነቢዩ አሰፋ ለፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

የፋብሪካው ግንባታ በ11 ሺህ 652 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሲሆን፥ ለ400 ኢትዮጵያውያን እና ለአምስት ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች የስራ እድል የሚፈጥር ነው ተብሏል።

22 ቶን መጫን የሚችል ተሳቢ፣ ከ45 እስከ 60 ቶን መጫን የሚችል ሰሚትሬይለር፣ ሲኖትራክ ከባድ የጭነት መኪና፣ መሬት ውስጥ ተቀባሪ እና ከመሬት በላይ የሚቀመጡ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ጋኖች እና ኢንጅነርድ የብረት ውጤቶች ፋብሪካው ያመርታል።

አቶ ነብዩ እንደተናገሩትም በአንድ ሽፍት 1 ሺህ 22 ቶን መጫን የሚችሉ ተሳቢዎችን፣ 300 ከ45 እስከ 60 ቶን መጫን የሚችሉ ሰሚትሬይለሮችን፣ 1 ሺህ ሲኖትራክ መኪናዎችን በአንድ ዓመት ያመርታል።

ምርቶቹም የገቢ ምርትን ሙሉ ለሙሉ ለመተካት እና ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲሁም ለምስራቅ አፍሪካ ገበያ የሚቀርቡ ናቸው።

በምረቃ ስነስርአቱም ከፍተኛ የመንግስት ስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ምንጭ

(ኤፍ.ቢ.ሲ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *