ህዳር 15፣ 2010

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለተኛውን ቦይንግ 787-9 ድሪምላይነር አውሮፕላን ባሳለፍነው ማክሰኞ መረከቡን አስታወቀ።

አየር መንገዱ የመጀመሪያን ተረክቦ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሁለተኛውን ቦይንግ 787-9 ድሪምላይነር አውሮፕላን መረከብ መቻሉንም ነው ያስታወቀው።

አዲሱ ቦይንግ 787-9 ድሪምላይነር አውሮፕላን “ለንደን” የሚል ስያሜ የተሰጠው መሆኑንም ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

አዲሱ አውሮፕላን የአየር መንገዱን የአውሮፕላኖች ብዛት ቁጥር 95 ያደረሰ ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 21 አውሮፕላኖች የድሪምላይነር አውሮፕላን ቤተሰብ ናቸው።

አየር መንገዱ የመጀመሪያውን አውሮፕላን በጥቅምት ወር ውስጥ መረከቡ ይታወሳል።

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 787-9 ድሪምላይነር አውሮፕላን በአሁኑ ጊዜ ወደ ኪሊማንጃሮ፣ ዛንዚባር፣ ሞምባሳ፣ አቡጃ፣ ማዳካስካር፣ ዱባይ እና ኒው ዴህሊ በረራ በማድረግ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡም በ1 ነጥብ 3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር አራት ቦይንግ 777 ለመግዛት መስማማቱ ይታወሳል።

አየር መንገዱ መቀመጫውን ቺካጎ ካደረገው የቦይንግ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ጋር ቦይንግ 777 ኤከስን ለመግዛት እየተነጋገረ እንደሚገኝም ታውቋል።

ስምምነት ከተደረሰባቸው አራት አውሮፕላኖች መካከል ሁለቱ፥ ባለፈው ሰኔ ወር በፓሪስ በተደረገው የአየር ትራንስፖርት አውደ ርዕይ ስምምነት የተደረገባቸው መሆኑ ተነግሯል።

ምንጭ

(ኤፍ.ቢ.ሲ)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *