በመንግስት እንደመፍትሄ የሚወሰደው የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ ከኢኮኖሚ ጉዳቱ በዘለለ የሰበአዊ መብቶች ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል ፡፡ አሁን ላይ ትርጉማቸው  እየሰፋ የመጡት የመሰብሰብና ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብቶችን ካለ ኢንተርኔት አገልግሎት ለመተግበር አዳጋች እንደሚሆንም ተጠቁሟል፡፡

በኢንተርኔት ሲሳይቲ አለምአቀፍ የኢንተርኔት ፖሊሲ ዳሬክተር እንደተናገሩት ትክክለኛ መፍትሄ የመረጃና የመረጃ ነጻነትን መገደብ ሳይሆን ፖለቲካዊ ችግሩን መፍታት ነው እረጅም ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም የተሸለ መፍትሄ የሚሆነው እሱ ነው ብለዋል፡

ከዚህ አንጻር የመንግስት የኢንተርኔትና የግንኙነት ፖሊሲዎች በሚቀረፅ ወቅት ፖለቲካዊ ሆኑ ቴክኒካዊ ምክንያቶችን ተከትለው የሚመጡ የኢንተርኔት መቋረጦች ከግምት ውስጥ ሊገቡ ይገባል ተብሏል፡፡ በየጊዜው የሚደረጉ የኢንተርኔት መቋረጦች  ከሰበአዊ መብት ጥሰት ባሻገር ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ተፅኖ እያሳደሩ እንደሚገኙና ባሳለፍናቸው ሁለት ዓመታት ብቻ ከሳህራ በታች የሚገኙ አገራት በኢንተርኔት መቋረጥ ምክንያት ሁለት ሰላሳ ሰባት  ሚሊዮን የሚተጋ ዶላር እንዳጡ ተገልጸል፡፡

በርካታ ፈተናዎችን ሚያስተናግደው የአፍሪካ የኢንተርኔት ዘርፍ ለአሀጉሪቱ ኢኮኖሚ ያለው አስተዋጾ  እጅግ አነስተኛ ሲሆን አሁን ላይ በአፍሪካ ከኢንተርኔት ዘርፍ እየተገኘ ያለው ገቢ 1.1 በመቶ ብቻ ነው፡፡

ዘርፉ በተለይም በኢትዮጵያ የተማረ የሰው ሀይል እጥረት የክህሎት ክፍተት የመሳሰሉት ችግሮች እንዳሉበት የተገለፀ ሲሆን ከፍተኛ የኢንተርኔት  ዋጋም አገሪቱ ከዘርፉ ተገቢውን ጥቅም እንዳታገኝ አድርጓታል ተብሏል፡፡

አሁን ላይ ከ52 መቶ በላይ የሚሆነው የአለማችን የኢንተርኔት ተጠቃሚ በመንግስ በሚደረጉ ኢንተርኔት መቋረጥ ውስጥ የሚያልፍ ሲሆን በ2016 ብቻ አለማችን 2.4 ቢለየን ዶላር ገቢ አጥታለች፡፡

ምንጭ

thiopiafirst.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *