ፕሮግራሞች ዝርዝር

ዓባይ ወቅታዊ ዜና ኤፍ ኤም መደበኛ ፕሮግራሞች ዝርዝር

. ዜናና ወቅታዊ

1.ዜና

በሀገሪቱ፣በአህጉሪቱና በአለም ዙሪያ የሚከሰቱና የሚፈፀሙ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ክንዋኔዎችን በመዳሰስ ወቅታዊና ሚዛናዊነትን የተላበሱ መረጃዎች የሚቀርብበት

ከሰኞ እስከ እሁድ

ጠዋት 2፡30   ቀን 6፡00

ማታ 12፤00 እና 3፡00

2 ሰሞኑን አለም

–በዓለማችን ከተከናወኑ አንኳር ጉዳዮችን ለሃገራችን ቀረብ ያሉና ትምህርት ሰጪ የሆኑ ጉዳዮን ቅድሚያ በመስጠት የተወሰኑትን መርጦ ሰፋ ብሎ የሚቃኝበት

ዓርብ ምሽት

ከ12፡30 እስከ 1፡00

3.ወቅታዊ ጉዳዮች፤

በሳምንቱ ከተከሰቱ አነጋጋሪ ጉዳዮች መካከል አንዱን በመምረጥ ስለ ጉዳዩ የሚተነትን ባለሙያ በመጋበዝ ህብረተሰቡ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ እንዲኖው ማድረግ

ሰኞ ማታ ከ2፡00-3፡00

 

. ማህበራዊ

1 ልሳነህግ

ከህግ ጋር ግንኙነት ያላቸው ጉዳዮች ዙርያ የሚያተኩርና በተሰጠው ፍርድ ዙርያና ሌሎች ህግ ነክ ጉዳዮችን በማንሳት ምላሽ የሚጥበት፣ ውሳኔ ያገኙ የፍርድቤት ክርክሮች ህብረተሰቡን እንዲማርበት የሚያደርግ ፕሮግራም

ሰኞ ጥዋት

ከ3፡00 እስከ 4፡00

  1. ስነልቦና

በእለተ ተእለት ኑሮ እንዲሁም በዘላቂ ህይወታችን ውስጥ የሚጋጥሙን የስነ-ልቦና ችግሮችን፣ በተጨማሪም በቤታችን፣ በጎረቤታችን ወይም በማህበራዊ መስተጋብራችን ውስጥ የሚጋጥሙን ችግሮችን ሞያዊ መፍትሔ የሚሰጥ ፕሮግራም ነው፡፡

ማክሰኞ ቀን

ከ 8፡00 እስከ 9፡00

  1. ምክረ ጤና

ስለ ጤንነትዎ የሚጠቅሙ ሞያዊ ምክሮችን በህክምና ባለሙያዎች የሚያገኙበት ሲሆን በተለይ ህ/ሰቡን የሚያስጨንቁ የህመም እና የበሽታ ዓይቶችን በማንሳት አድማጮች በቤታቸው ሆነው መፍትሔ የሚገኙበት ፕሮግራም

ረቡዕ ረፋድ

ከ4፡00 እስከ 5፡00

4 የህናት ጉዳይ

ልዩ ድጋፍ የሚስፈልጋቸውን ህጻናት የምንዳስስበት የተለያዩ የመብት ጥሰቶችና መፍትሔዎቻቸውን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምክክር የሚደረግበት ህጻናት በስነ-ምግባር ታንፀው እንዲያድጉ የሚረዱ ስነልቦናዊ ምክሮችን ለወላጆችና ለአሳዳጊዎች የምንለግስበት ዝግጅት ነው

ሐሙስ ረፋድ

ከ4፡00 እስከ 5፡00

 

5.የመንገድ ትራፊክ ደህንነት

ህ/ሰቡን ራሱን ከትራፊክ አደጋ የሚጠብቅበትን እና እንዲከላከል እንዲሁም የወጡ የትራፊክ ህጎችን በማክበር አሽከርካሪም እግረኛም ግንዛቤ አግኝተው ራሳቸውን ከአደጋ እንዲከላከሉ የሚያስተምር በቀጥታ የስልክ ውይይት የሚተላለፍ ነው፡፡

ሰኞ ማታ

ከ1፡00 እስከ 3፡00

  1. አሸናፊነት

በአካል ጉዳተኝነት ዙርያ የሚሰራ ፕሮግራም ሲሆን ስለ አካል ጉዳተኞች የግንዛቤ የሚስጨብጥ፣ እያዝናና የሚያስተምርና ስኬታማ የሆኑ አካል ጉዳተኞች ተሞክራቸው የሚቀርቡበት ዝግጅት ነው

ዓርብ ከሰዓት

ከ10-12 ሰዓት

7.የወጣቶች ጊዜ

ወጣቶች ምክንያዊነት እንዲሆኑ፣ ልዩነቶች በዲሞክራሲያዊ መንግድ የመፍታት ባህል እንዲያዳብሩ፣ ስራ ፈጣሪነት በጽናት ተግባራዊ እንዲያደርጉ፣ ስደትን መፍትሄ እንዳልሆነ እንዲያምኑ፣ የኃላቀርነት አስተሳሰብ አንቅሮ እንዲተፉ በማድረግ በሱስ እንዳይጠመዱ የሚያግዝ ፕሮግራም

ቅዳሜ ረፋድ

ከ5፡00 እስከ 6፡00

  1. አስኳላው

ወጣቱ ትውልድ የተማረና ሃገር ተረካቢ ትውልድ እንዲሆን በመማር ሂደቱ የሚገጥሙትን ችግሮች እንዴት ባለ መልኩ እየፈታን ከመምህራና ወላጆች ጋር ተጣምሮ መሄድ እንዳለበት መንገድ ማመላከት፣ ት/ቤት ሌላው ትንሿ ኢትዮጵያ እንደመሆኑ መጠን እዛ በሚቆይበት ግዜ በቀጣይ ሃገር እንዴት መገንባት እንደሚችል ተጠናክረው የሚወጡበትን መንገድ እንዲይዙ ለማስቻል በቀጣይነት ከሚኒ ሚዲያው ጋር በመቀናጀት የሚሰራ

ቅዳሜ ረፋድ

ከ4፡00 እስከ 5፡00

9.ትዳር እንዴት ነው

የተለያዩ ቤተሰባዊ ጉዳዮች ተነስተው ስለ ትዳር፣ ልጆች እና ተያያዥ ጉዳዮች የሚወያዩበትና ሀሳብ የሚለዋወጡበት የቀጥታ ስልክ ውይይት ነው

ቅድሜ ምሽት

ከ1፡00 እስከ 3፡00

  1. 1 አረንጓዴ ኢኮኖሚ

የሃገሪቱን ኢንዱስትሪና አረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ የሚቃኝበት፣ የአረንጓዴ ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች አተገባበር በዘርፉ ያሉ የኢትዮጵያ ስኬቶችን የተመለከተ የተለያዩ ዶክመንተሪዎችና ባለሙያዎች የሚቀርቡበት

ረቡዕ ጥዋት

ከ3፡00 እስከ 4፡00

 

. ፖለቲካዊ

1 መፍትሄው ምንድነው

ህብረተሰቡ ያለውን ጥያቄ ያለምንም ፍርሃት የሚጠይቅበት፣ ሀሳቡን በነጻነት የሚገልጽበት፣ መፍትሔ የሚሹ ጉዳዮች የሚነሱበት ልዩ መድረክ ነው፡፡ ቅሬታ አቅራቢ ቅሬታውን የሚያቀርብበት ተጠያቂው አካል በስቱዲዮ ተገኝቶ ወይም በቀጥታ የስልክ መስመራችን ምላሽ የሚጥበት

እርብ ረፋድ

ከ4፡00 እስከ 6፡00

2 .ክልሎቻችን በዓባይ ሲቃኙ

— በውስጡ በርካታ ርዕሰ ጉዳዮ የሚያጠቃልል ሲሆን ከዚህ መካከል የክልሉ አወቃቀር፣ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ፣ ባህልና ታሪካዊ እሴቶች፣ የአኗኗር ዘይቤ፣ የመሰረተ ልማት እንቅስቃሴ፣ ማህበራዊ ልማት ማስፋፋት፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና ችግሮቹን ለመፍታት እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ እና ሌሎች የክልሉ ልዩ ልዩ መገለጫዎች በጥልቀትና በስፋት ይዳሰስበታል፡፡

ረቡዕ ረፋድ

ከ5፡00 እስከ 6፡00

. ኢኮኖሚያዊ

1.ዓባይ1 እና 2

ሜጋ ፕሮጀክቶችን የሚዳስስ ዝግጅት ሲሆን በሃገሪቱ ውስጥ በሚከናወኑ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የያዘው ወጣቱ አካል እንደመሆኑ መጠን በዚህ ወጣት ትውልድ እየተሰሩ፣እየተገነቡ፣እየተነደፉ ያሉትን ማንኛውም የልማት ስራዎችን አጉልቶ በማሳየት ዓባይ ግድብን ከንድፍ እስከ የግንባታ ስራ ክንውን ድረስ በሺህዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች እየሰሩት እንዳለ ማሳየት፣

ዓባይ1 ሰኞ ረፋድ ከ4፡00-5፡00

ዓባይ2 አርብ ቀን ከ9፡00-10፡00

  1. ኢትዮ ቢዝነስ

የቢዝነስ እና ኢኮኖሚ መረጃዎች፣ ምርጥ ተሞክሮችንና ፍልስፍናዎችን በመተንተን ጠቃሚ እውቀቶችን የሚያካፍል ፕሮግራም

ሰኞ ቀን

ከ 7፡00 እስከ 8፡00

 

. መዝናኛ

1.ቢያውቁት ይመልሱ

-አድማጮች በቀጥታ ስልክ የሚሳተፉበት የሚያውቁትን የሚመልሱበት የማያውቁትን ለማሳወቅ የሚዘጋጅ ፕሮግራም ሲሆን የንባብ ባህልን ለማዳበር የሚረዱ የተለያዩ ጥያቄዎች የቀርቡበታል

ማክሰኞ ረፋድ

ከ4፡00 እስከ 6፡00

2.ዓባይ እስከረፋድ

በውስጡ ትረካ፣ የተለያዩ መረጃዎች፣ ዜና፣ ትዝብት እና ሌሎም አጫጭር መረጃዎችና መዝናኛዎች የያዘ ስዓት

ከሰኞ እስከ አርብ ማለዳ

ከ12፡00 እስከ 2፡30

3.ዓባይ መዝናኛ

ኪነ-ጥበብ፣ ተፈጥሮ፣ ወቅታዊ ጉዳይ እና ስነ-ልቦና ያካተተ የመዝናኛ ዝግጅት ነውቀን

እሁድ ከሰዓት

ከ9፡00 እስከ 11፡00

4.የፍቅር ጊዜ

ፕሮግራሙ በዋነኝነት ከፍቅር ጋር የተገናኙ ጉዳዮችን በማንሳት ያወያያል፣ በጉዳዩ ላይ የስነ-ልቦና ባለሙያዎችን ሙያዊ ምላሽ አካቶ የሚቀርብ፣ እንዲሁም የፍቅር ታሪኮች፣ ደብዳቤዎች፣ ግጥሞችና ሌሎችንም ያካተተ ፕሮግራም ነው፡፡

እሁድ ምሽት

ከ3፡30 እስከ 5፡30

5.ኢትዮጲያዬ

ህብረቀለማዊ ስብጥራችን፣ ውበታችን፣ ታሪካአወን እና ቅርሳችን፣ መኩሪያችን ኢትዮጵያዊነታችን ማንነታችን መሆኑን የሚያሳይ፣ በውብ መልክዐ ምድራችን እየተዘዋወርን ቃኝተን የምናስቃኝበት ሳምንታዊ ፕሮግራም ነው፡፡ ፕሮግራሙ ሃገራዊ በሆኑ እሴቶቻችን ላይ በሞያና በዕውቀት ደረጃቸው የተመረጡ ስራዎች ይዘን የምንቀርብበት ፕሮግራም

ሀሙስ ቀን

7፡00-8፡00 ሰዓት

6.ባላገሩየተለያዩ ብሄር ብሄሰብ ዜማዎች ከመረጃ ጋር የሚቀርቡበት የመዝናኛ ፕሮገራም

ረቡዕ ከሰዓት 10-11 ሰዓት

7.ዘመንን በዜማ

ቆየት ያሉ ዜማዎች ከመረጃ ጋር የሚቀርቡበት የመዝናኛ ፕሮገራም

ማክሰኞ ማታ ከ4-5 ሰዓት

8- -.የአፍሪካ ሙዚቃ

የተለያዩ የአፍሪካ ሙዚቃዎች ከመረጃ ጋር የሚቀርብበት የመዝናኛ ፕሮገራም

ሰኞ ማታ ከ4-5ሰዓት

9.የልጆች ጊዜ

ህጻናት በራሳቸው አንደበት የሚቀርቡበትና የሚያቀርቡት የመዝናኛ ዝግጅት

እሁድ ጥዋት

ከ3፡00 እስከ 3፡30